የኢትዮጵያዊያን ፡ መድርክ
ምክር እስከመቃብር
|
ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
|
ትምህርትና እውቀት:
|
|
ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች
ከሕይወት እምሻው
ታዋቂው የባህል ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው ‹‹ያኮራናል፤ በሀገራችን ውብ ባህል ሞልቶናል›› እያለ ሲዘፍን በቴሌቪዥን አየሁ፡፡ ነጭ የሀበሻ ልብሱን ከነነጭ ጫማው ግጥም አድርጎ፤ በዛ ላይ ደግሞ ግሩም ካባ ደርቦ እየተወዘወዘ ይዘፍናል፡፡ ዘፈኑ እንደተጀመረ ሰማኸኝ ‹‹ኢትዮጵያ››ን ሲጠራ በ ‹‹ጵ›› ፈንታ ‹‹ፒ››እየተካ ሲዘፍን ሰማሁት፡፡
ይባስ ብሎ ይደጋግመው ጀመር፤ ‹‹ኢትዮፒያ!›› ... ይህን ልብስ ለብሶ ስለ ውብ ባህላችን መትረፍረፍና ስለኩራታችን እያወራ ደጋግሞ ‹‹ኢትዮፒያ›› ይላል፡፡ ኢትዮጵያን በ‹‹ፒ›› የሚጠሩ ብዙ ‹‹ኢትዮፒያውያን›› ን አውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ በሆነ ቢራ ማስታወቂያ ላይ ‹‹ የኢትዮፒያውያን ኩራት፤ የሀገሬ ድንቅ ሀብት›› እንደምትለዋ ልጅ፡፡ (በነገራችን ላይ እሱን ማስታወቂያ በአየሁ ቁጥር ‹‹ጵ›› ማለት ተራራ የሆነባት ልጅ ‹‹ቅ›› ማለቷ ይገርመኝና ከተሞላቀቀች አይቀር ‹የኢትዮፒያውያን ኩራት፤ የሀገሬ ‹‹ድንክ›› ሀብት›› ብላ ትርምስምሱን አውጥታው ቢሆንስ ኖሮ ብዬ አስባለሁ!) ይሄው፤ በሷና በመሰሎቿ ተገርሜ ሳላበቃ የባህል ድምፃዊውም ሀገሩን በፈረንጅኛ ጠራ፡፡ ‹‹ፓስታ ለመሆን የሚጥሩ ድፎ ዳቦዎች›› አለ ያ አዳም ረታ! |
የት ነህ እና ፍርፍር ባይበዛበት ትዳርስ ጥሩ ነበር
ከሕይወት እምሻው አንድ ባለትዳር ጓደኛዬ ነው፡፡ በአንዱ የአዘቦት ቀንከስራ በኃላ ሌላ ጓደኛው ይደውልለትና ‹‹የት ነህ?›› ይለዋል፡፡ ...‹‹ፀጉሬን እየተቆረጥኩ›› ብሎ መለሰ፡፡ ‹‹ያምሃል. . !? እንዴት በአዘቦት ቀን ፀጉርህን ትቆረጣለህ?›› ነገሩ ያልገባው ጓደኛዬም፤ ‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››ሲለው፤ ‹‹ቅዳሜ እና እሁድ በምን ሰበብ ከቤት ልትወጣ ነው!?››ብሎ ይመልስለታል፡፡ ቀጠል አድርጎም፤ ‹‹ ይኸውልህ ወዳጄ፤ በጠዋት ፀጉሬን ልቆረጥ ብለህ ትወጣና አንዴ ወረፋ በዛ እያልክ፣ አንዴእገሌ መጥቶ ሻይ ቡና እያልን ነው ብለህ እስከ ማታ ትቆያለህ እንጂ እንዲህ ያለ ወርቅ ከቤት መውጫ ምክንያት በአዘቦት ቀን ታባክናለህ?››ብሎ አስረዳው፡፡ ይህን ሲነገርኝ ‹‹‹የት ነህ?› እና ፍርፍር ባይበዛበትትዳርስ ጥሩ ነበር›› የሚለው በአንድ ወቅት ፌስቡክ ላይ ያነበብኩት አባባል ትዝ አለኝ፡፡ በትዳር ወስጥ ወንዶችከሚማረሩባቸው ነገሮች አንዱ ለራስ ጊዜ ማጣት ነው፡፡ ‹‹የት ነህ?›› ‹‹ከማን ጋር ነህ?›› ‹‹ስንት ሰዓት ትመጣለህ?››‹‹መሽቷል ቶሎ ና›› ሲበረታም ‹‹ያመሸህበት እደር!›› የተለመዱ የሚስቶች ጥያቄዎችና ማስፈራሪያዎች ናቸው፡፡ የ‹የት ነህ?› ቁጥጥሩ የጋብቻን ፈረስ ተከትሎ የሚመጣጋሪ ነው፡፡ አንዱ ጓደኛዬ እንደነገረኝ፤ ‹‹ከተጋባን በኃላ ሚስቶቻችን እኛን እንደ ባል እና እንደ ልጆቻቸው አባት ከማየት ይልቅየወለድናቸው ልጆች ታላቅ ወንድም የሆንን እስኪመስል ድረስ እንደልጅ ሊያዝዙና ሊመሩን ይፈልጋሉ፡፡ አሁን እስቲ ወንድ ልጅ ከስራእንደወጣ እየበረረ ቤት መሄዱ ምን ያስፈልጋል? አያጠባ!›› ብሎኛል፡፡ ወንዶቹ በዚህ ሲማረሩ ሴቶቹ ደግሞ ‹‹ባል መች እቤትይቀመጣል! ገና ሲነጋ የሚወጣበትን ሰበብ ያብሰለስላል›› እያሉ ይብሰለሰላሉ፡፡ ‹‹በየደቂቃው እየደወልን ‹የት ነህ?› የምንለውወደን አይደለም፡፡ እንደዛ ካላልናቸው የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ፡፡›› የሚሉ ሴቶችም ጥቂት አይደሉም፡፡ ‹‹ወንድ ልጅ ገደብ ካላሳዩት ገደብ አያውቅም፡፡ እስከ3 ሰዓት ማምሸቱን ብፈቅድለት እስከ 6 መቆየት ይፈልጋል›› ይላሉ፡፡ እርግጥ ትዳር የሚያዘው አብሮ መሆንን ነው፡፡ ሆኖም ትዳርውስጥ ያሉት ሰዎች ቢጋቡም፣ ቢወልዱም አሁንም ሁለት ሰዎች ናቸው፡፡ በዕውቀቱ ስዩም እንዳለው፤ ባልና ሚስት አንድ ቢሆኑም፤ ታክሲውስጥ የሁለት ሰው ሂሳብ መክፈላቸው ግን የማይቀር ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት፤ የራሳቸው ጓደኞች፣ ስራ፣ የግላቸውጊዜ ማሳለፊያ፣ ከሁሉም በላይ የራሳቸው የሚሉት ጊዜ ሲኖራቸው ትዳራቸውይጠቀማል እንጂ አይጎዳም፡፡ ባልና ሚስት ለብቻቸው የሚሆኑበት ጊዜ ቢያስፈልጋቸውም ነጋ ጠባ አብሮ አድሮ፣ አብሮ ውሎ፣ አብሮ ሰርቶ፣ አብሮ ወጥቶና ገብቶ መልሶአብሮ ማደሩ ግን መነፋፈቅን አጥፍቶ ትዳርንም ሊያጠፋ ይችላል ባይ ነኝ፡፡ እናም ሴቶቹ የ ‹የት ነህ?› ጭቅጭቁ ላይ ፤ ወንዶችደግሞ በሌሊቱ ከቤት ማምለጫ ሰበብ ፍለጋው ላይ ላላ ብናልስ? |
የድሮ ትውሰታዎች
|
|
|
|